
Monetize Telegram Mini App with Telega.io
Connect your app, set CPM, and watch your revenue grow!
Start monetizing
17.7

Advertising on the Telegram channel «ETHIO-UNIVERSITY»
5.0
34
Education
Language:
English
1.9K
9
Share
Add to favorite
Buy advertising in this channel
Placement Format:
keyboard_arrow_down
- 1/24
- 2/48
- 3/72
- Native
- 7 days
- Forwards
1 hour in the top / 24 hours in the feed
Quantity
%keyboard_arrow_down
- 1
- 2
- 3
- 4
- 5
- 8
- 10
- 15
Advertising publication cost
local_activity
$4.80$4.80local_mall
0.0%
Remaining at this price:0
Recent Channel Posts
imageImage preview is unavailable
🔔 የመውጫ ፈተና የመጀመሪያ ቀን የኦንላይን ፈተና ውሎን ተከትሎ ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ ማሳሰቢያ፦
✅ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናውን ሲጨርስ Finish and Submit ሳያደርግ መውጣት የለበትም። ተፈታኙ ይህንን ማድረጉንም በፈተና ክፍሉ የተመደበ ባለሙያ ማረጋገጫ ሳይሰጠው እና ተፈታኙም ፈተናውን መጨረሱን በፊርማው ሳያረጋግጥ ከመፈተኛ ክፍል መውጣት አይኖርበትም።
✅ በተለያየ ምክንያት ሲስተም ዘጋብን በማለት ፈተና ክፍል ውስጥ የሚቀመጡ ተፈታኞችን በተለያዩ መንገዶች የማጣራት ሥራ በመስራት አስፈለጊውን የእርምት ወይም አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰድ ይኖርበታል።
(ሚኒስቴሩ ለዩኒቨርሲቲዎች ያስተላለፈው ሙሉ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)
https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts
1949
18:03
09.06.2025
imageImage preview is unavailable
#ModelExam
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በኦንላይን ለሚወስዱ ተማሪዎች #ሞዴል ፈተና በተለያዩ ቦታዎች እየተሰጠ ነው፡፡
#ሞዴል ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት እንዲሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መርሐግብር ማዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡
ሞዴል ፈተናው መልቀቂያ ፈተናውን በሁለት ዙር በኦንላይን የሚወስዱ ተማሪዎች አስቀድመው በተለያዩ የመፈተኛ ጣቢያዎች በመገኘት ልምምድ እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
ምስል፦ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts
2616
10:51
29.05.2025
imageImage preview is unavailable
ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይዘጋጁ!
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
ለሀገር አቀፍ ፈተናው እየተዘጋጁ ነው?
ተፈታኝ ተማሪ ከሆኑ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ለፈተናው በቂ ዝግጅት ለማድረግ የሚያስችሉ ትምህርቶችን ማግኘት ይችላሉ።
በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጁ የቲቶርያል ቪዲዮዎችን ለማግኘት 👇
https://examinfo.moe.gov.et/guides
https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts
2862
07:17
29.05.2025
#ETA
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ሚሽከን ኮሌጅ ላይ አስፈላጊው የህግ እርምጃ እንዲወሰድበት ጠየቀ፡፡
ባለሥልጣኑ ከዚህ ቀደም በኮሌጁ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ የትምህርት ተቋሙ ተግባራዊ ባለማድረጉ የህግ እርምጃ እንዲወሰድበት መጠየቁ ታውቋል፡፡
ሚሽከን ኮሌጅ በዋና ማዕከሉ አዲስ አበባ እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ማለትም በባሌ ሮቤ፣ ሀዋሳ፣ አርባምንጭ፣ ሳውላ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ጋምቤላ፣ ጊምቢ፣ ጅማ፣ ሆሳዕና፣ ነቀምቴ፣ ቴፒ፣ ጀግጅጋ፣ ቻግኒ እና ባህር ዳር ቅርንጫፎቹ በቅድመ-ምረቃ ደረጃ ከሐምሌ 2004 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2007 ዓ.ም ፈቃድ ባገኘባቸው ከተሞች እና የትምህርት መስኮች በርቀት መርሐግብር ሲያስተምር መቆየቱን ባለሥልጣኑ አስታውሷል፡፡
በፈፀመው የህግ ጥሰት ምክንያት ማስተማሩን አንዲያቋርጥ ተደርጎ እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ የተቀበላቸውን ተማሪዎች እንዲያስጨርስና በህጋዊ አግባብ የተመረቁ ተማሪዎችን መረጃ ፈቃድ ወዳለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በማዘዋወር ለባለሥልጣኑ ሪፖርት እንዲያደርግ በተደጋጋሚ መጠየቁን ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡
ይሁን እንጂ "ኮሌጁ ከባለሥልጣኑ የተወሰነበትን ውሳኔ ተግባራዊ ባለማድረግ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ተሰማርቶ ዜጎች ላይ ሁለንተናዊ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ" ከዚህ ተግባሩ እንዲቆጠብ እና የከፍተኛ ትምህርት አገልግሎት መስጠት እንዲያቆም አስፈላጊው የህግ እርምጃ እዲወሰድበት ባለሥልጣኑ ለሁሉም ክልላዊ መንግሥታት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤቶች፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ጽ/ቤት፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲቨል ሰርቪስ ኮሚሽን እና ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ከ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት በጻፈው ሰርኩላር ጠይቋል፡፡
https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts
2204
11:58
28.05.2025
“ ለሦስት አሸናፊዎች እስከ 20 ሺሕ ዶላር ሽልማት ተዘጋጅቷል ” - ሄፈን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ
500 ወጣቶችን የሚያሳትፍ፣ ሦስት አሸናፊዎችን እስከ 20 ሺሕ ዶላር የሚያሸልም የግብርና ቴክኖሎጂ ሥራ ፈጠራ ውድድር ማዘጋጀቱን ሄፈር ኢትዮጵያ ገለጸ።
ውድድሩ፣ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን፣ የአርሶ አደሮችን ሕይወት ለማሻሻል፣ የወጣቶችን የቴክኖሎጂ ፈጠራ አቅም ለማጎልበት ዓላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል።
የፈጠራ ክህሎት ያላቸው ወጣቶች ከዛሬ (ግንቦት 13/2017 ዓ/ም) ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአዩቲ ድረገጽ በኦንላይን መመዝገብ እንደሚችሉ ድርጅቱ ጠቁሟል።
የእድሉ ተጠቃሚ ለመሆን በየትኛውም ክልል ያሉና የግብርና ቴክኖሎጂ ሥራ ፈጠራ የማቅረብ አቅሙ ያላቸው ወጣቶች መሳተፍ እንደሚችሉም አዘጋጆቹ አብራርተዋል።
ሽልማቱን የሚያገኙት እነማን ናቸው ?
ከሚቀርቡት 500 የፈጠራ ውጤቶች መካከል በጣም የተሻሉ ተብለው የሚመረጡ ሦስት የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለቤቶች የሽልማቱ አሸናፊዎች ይሆናሉ።
በዚህም ፦
- አንደኛው አሸናፊ 10 ሺሕ ዶላር
- ለሁለተኛ አሸናፊ 6, 500 ዶላር
- ሦስተኛው አሸናፊ ደግሞ 3, 500 ዶላር ይሸለማሉ ተብሏል።
ውድድሩን አሸናፊዎችስ በተዋረድ እንዴት ይለያሉ ?
ይቀርባሉ ተብለው ከሚጠበቁት 500 ገደማ የግብርና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ሥራዎች መካከል 30ዎቹ ልምድ ባላቸው ዳኞች ተገምግመው ይመረጣሉ።
30 የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችም ተወዳድረው የሚያሸንፉ 10 የፈጠራዎች ባለቤቶች ለአምስት ቀናት ስልጠና ይወስዳሉ። 10 የሚሆኑት ደግሞ ለመጨረሻ ውድድር ቀረበው ሦስቱ አሸናፊዎች ይመረጣሉ።
ኦንላይን መመዝገቢያው https://ayute-ethiopia.et መሆኑ ተጠቁሟል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts
1586
05:42
22.05.2025
imageImage preview is unavailable
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ተደረገ።
የ2017 ትምህርት ዘመን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ / የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት መርሃ ግብር ይፋ ተደርጓል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋ ባደረገው መርሃ ግብር ፈተናው ከሰኔ 23/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም የሚሰጥ ይሆናል።
በወረቀት የሚፈተኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 21 እና 22/2017 ዓ/ም እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 29 እና 30/2017 ዓ/ም ወደሚፈተኑበት ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ይሆናል፡፡
በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተፈታኞች ከመኖሪያ ቤታቸው በየቀኑ እየተመላለሱ በተመደቡበት መፈተኛ ማዕከል የሚፈተኑ ሲሆን ዝርዝር መርሃ ግብሩ ከላይ ተያይዟል።
የፈተናው ይዘት በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያተኮረ በመሆኑ እያንዳንዱ ተፈታኝ በትምህርት ቤቱ የተማረበትን የተማሪ መጽሐፍ መሠረት አድርጎ ተገቢ የሆኑ አጋዥ መጽሐፍትን ለበለጠ እውቀትና መረዳት በመጠቀም እንዲዘጋጅ አገልግሎት ጥሪ አስተላልፏል።
በፈተና ወቅት ለፈተና ስርቆትና ኩረጃ የሚውሉ ማንኛውንም ቁሳቁሶች መጠቀም የተከለከለ ነው ተብሏል።
መረጃው ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተላከ ነው።
https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts
1754
15:34
09.05.2025
imageImage preview is unavailable
#Reminder
የፋይዳ መታወቂያ አውጥተዋል?
በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ተፈታኞች የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ሊያወጡ እንደሚገባ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል።
የመንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
የመውጫ ፈተናውን ለመውሰድ ምዝገባውን በጊዜ በማድረግ የፋይዳ መታወቂያዎን ይያዙ።
https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts
3223
14:18
25.04.2025
በዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ የሚገኘው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት "በኢትዮጵያ መልቀቂያ የብሔራዊ ፈተና ውጤት የቅርብ ጊዜ ተለዋዋጭነት ግምገማ" በሚል ርዕስ ለአንድ ዓመት የቆየ ጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል።
ኢንስቲትዩቱ ካቀረባቸው የፖሊሲ ምክረ ሐሳቦች መካከል፣ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ የሚገኘው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይሰጥ የሚለው ይገኝበታል፡፡
በኢንስቲትዩቱ የማኅበራዊ ልማትና አካታችነት ማዕከል ኃላፊና ከፍተኛ ተመራማሪ ደሳለኝ አንጭሶ (ዶ/ር)፥ የተማሪዎች ውጤት እንዲቀንስ ካደረጉ ቁልፍ ምክንያቶች መካከል የፈተና አሰጣጥ ስርዓቱ መቀየር በተለይ ከከተሞች ራቅ ካሉ አካባቢዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚመጡ ተማሪዎች ላይ የፈጠረው የስነ-ልቦና ችግር ተጠቃሽ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተፈጠረው የስነ-ልቦና ችግር ምክንያት ጥሩ ውጤት ማምጣት የነበረባቸው ተማሪዎች ውጤት ሳያመጡ መቅረታቸው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡
"ተማሪዎች የባዮሜትሪክ መረጃዎች እንዲሞሉ በማድረግ እንዲሁም በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የደኅንነት ካሜራዎችን በመግጠም የቁጥጥር ስራ በመስራት፣ ተማሪዎች ከሚኖሩበት አካባቢ ሳይርቁ ፈተናውን እንዲፈተኑ ትምህርት ሚኒስቴር የረዥም ጊዜ ዕቅድ ይዞ እንዲሠራ" ምክረ ሐሳብ መቅረቡን ገልፀዋል።
የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ማሻሻል እና ከታች ጀምሮ ጥራት ላይ ሊሰራ እንደሚገባ የገለፁት ኃላፊው፤ የትምህርት ቤት አመራሮች ዕውቀትን መሠረት ባደረገ ሁኔታ ሊመደቡ እንደሚገባም ምክረ ሐሳብ መቅረቡን ተናግረዋል።
በማኅበረሰቡ ዘንድ "ትምህርት ምን ያደርጋል" የሚል ዕሳቤ መቀየር ላይ አፅንኦት ሰጥቶ የለውጥ ሥራ መስራት ይገባል የሚለው በጥናቱ የተለየ ምክረ ሐሳብ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ጥናቱ በፀጥታ ችግር ምክንያት የአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎችን እንዳላካተተ ተገልጿል። #Reporter
https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts
4626
14:22
08.04.2025
" 10ኛ ክፍል ላይ ሀገር አቀፍ ፈተና ሳይወስዱ ወደ 11 የተዘዋወሩ ተማሪዎች ልዩ የማካካሻ ትምህርት ሊሰጣቸው ይገባል፣ ካልሆነ ግን መውደቅ ይቀጥላል " - ትምህርት ሚኒስቴር
ትምህርት ሚኒስቴር ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር በየጊዜው በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ መሆኑን ተከትሎ አካሄድኩት ባለው እና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ጥናት ዘርፈ ብዙ ችግሮች መገኘታቸውን ገልጿል።
የትምህርት ዘርፍ ሪፎርም ከተካሄደ በኋላ ትምህርት ቤቶች ማስተማር ከሚችሉት በላይ ተማሪዎችን ያስተምራሉ ያለ ሲሆን ከዚህ በፊት 10ኛ ክፍል ይሰጥ የነበረውን ፈተና በመቅረቱ ሳይፈተኑ 11ኛ ክፍል መግባታቸው ለችግሩ ዋና ተጠቃሽ ምክንያት መሆኑን አመላክቷል።
በትምህርት ቤቶች በሚሰጠው የሞዴል ፈተና እና ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው የሀገር አቀፍ ፈተና ሰፊ ልዩነት እንዳለውም ገልጿል።
" በማህበራዊ እና በተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መካከል የማለፍ ንፅፅር ሲታይ ልዩነት አለ " ያለው ሚኒስቴሩ " የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት በማምጣት ወደ ከፍተኛ ተቋም ይገባሉ፣ ይሁን እንጂ በቂ አይደለም፣ ብዙ ነገሮች መሻሻል እንዳለባቸው ጥናቱ አሳይቶናል " ብሏል።
ጥናቱ ምን አይነት የትምህርት ዘርፍ ችግር ነው ይሄን ያክል ውድቀት ያመጣብን ፣ ከተማሪዎች መውደቅ እና ማለፍ ጋር ተያይዞ የትምህርቱ ባህሪ ምንድን ነው የሚለውን እና በአጠቃላይ በትምህርት ዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን የያዘ ነው።
በሁሉም የትምህርት ዘርፍ ላይ ያሉ ችግሮችን ያሳየው ይሄ ጥናት በመጨረሻም የመፍትሄ ሃሳቦችንም አቅርቧል።
ትምህርት ሚኒስቴር ምን የመፍትሄ ሃሳብ አቀረበ ?
" ከዚህ በፊት 10ኛ ክፍል ላይ ይሰጥ የነበረውን ሀገራዊ ፈተና ሳይወስዱ 11ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች ልዩ የማካካሻ ፕሮግራም ያስፈልጋቸዋል። ይሄ ካልሆነ ግን መውደቅ ይቀጥላል ፣ ምክንያቱ የሚፈለገውን ያህል እውቀት እና ክህሎት ይዘው አይወጡም።
በገጠር በተለይም በአርብቶ አደሮች አካባቢዎች ላይ ያለው የትምህርት ዘርፍ ልማት አነስተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እጅግ ወደ ኋላ እየቀረ ስለሆነ ማካካሻ መሰራት አለበት።
ሌላው ደግሞ ከትምህርት አመራር፣ መምህራን እና ከአቅም ግንባታ ጋር ተያይዞ ያሉ ጉዳዮች ውጤት በሚያመጡ ጉዳዮች ላይ ብቻ ትኩረት ተደረጎ የትምህርት አመራሩ አቅም እስካልሰጠ ችግሮቹ ይቀጥላሉ።
ለመምህራን የደመወዝ ጭማሪ ብቻ ሳይሆን መምህሮችን የሚያቅፍ የ insensitive package እስካልመጣ ድረስ ችግሮቹ ይባባሳሉ።
በተጨማሪም በሀብት ክፍፍል ላይ ክፍተት በመኖሩ በትምህርት ዘርፉ ልማት ላይ ተግዳሮት መኖሩን ያሳያል፣ ይሄም መፈታት አለበት " ሲል መፍትሄ ያለውን ሃሳብ አቅርቧል።
ትምህርት ሚኒስቴር ጥናቱን ባቀረበበት ወቅት የህዝብ ተወካዮች የተለያዩ አስተያየቶች፣ ጥያቄዎች እና ሃሳቦችን አቅርበዋል።
በጥናቱ ላይ የመፍትሄ ሃሳቦች መቅረባቸው ጥሩ ሁነው ሳለ እንደዚሁ ተወርተው መሬት ላይ ሳይወርዱ ከቀሩ ትርጉም አልባ ናቸው፣ በመሆኑም ሁሉም በአፅንኦት ሊመለከተው እንደሚገባ በተወካዮች ተጠቁሟል።
ከ1 እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የሚደረገው ድጋፍ አነስተኛ ነው፣ ይሄም አሁን ላለንበት ውጤት ማጣት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል ፤ በጥናቱስ ላይ ለምን ይሄ ሳይካተት ቀረ፣ ምክንያቱም የትምህርት መሰረቱ ከታች ጀምሮ ስለሆነ የሚሉ ጥያቄዎች ተነስቷል።
የተለያዩ ተማሪዎች በህገወጥ መንገድ ወደተለያዩ ሀገሮች እየተሰደዱ ነው፣ ተማሪዎች ይሄ ሲፈጠር ተረጋግተው መማር እየቻሉ አይደለም፣ ትምህርት ሚኒስቴር ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ተብሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts
4433
21:03
03.04.2025
#MoE
የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ለአንድ ዓመት እንዲያስተምሩ ሊገደዱ ነው።
ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ማኅበረሰቡን ለአንድ ዓመት በቅድሚያ እንዲያስተምሩ ወይም እንዲያገለግሉ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታወቀ።
ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ዝቅተኛ የሆነበትን መንስዔ በተመለከተ ጥናት አቅርበዋል።
ውይይት ሲደረግ ነበር።
በዚህም ወቅት በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ስለተያዘው እቅድ አብራርተዋል።
ላለፉት ዓመታት (እሳቸው በኃላፊነት ከተሾሙ ጀምሮ) ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት በከፍተኛ ደረጃ ዝቅተኛ እንዲሆን ካደረጉ መንስዔዎች መካከል፣ የመምህራን ብቃትና የተነሳሽነት ማነስ ተጠቃሽ መሆናቸው ጠቁመዋል።
ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እንዲቻል የተለያዩ ተግበራት እየተሰሩ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
'' የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ '' የሚል መጠሪያ የተሰጠው አሠራር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ዕቅድ የተያዘ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ " በአራት ዓመት የሚመረቅ ተማሪ፣ የሦስተኛ ዓመት ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ አስተማረው ማኅበረሰበብ ተመልሶ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ይሰጥና (ማኅበረሰቡን እንዲያገለግል ይደረግና) እንዲመረቅ ይደረጋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ይህም ሲሆን የተማሪዎቹ መሠረታዊ ወጪ የሚሸፈን እንደሚሆንም አክለዋል።
ይህ አሰራር ለተማሪዎች ለራሳቸው የተግባር ትምህርት እንደሚሆንና የበለጠ እንዲበስሉ እንደሚያደርጋቸውም ተናግረዋል።
ተማሪዎች የመምህርነትን ሙያ ተላብሰው በዚያው ወደ ሙያው እንዲያመሩ ዕድል በመፍጠር ለጊዜውም ቢሆን በዘርፉ እየቀነሰ የመጣውን ወደ ሙያው የሚገባ የአስተማሪን ቁጥር ለማሳግ እንደሚረዳም ሚንስትሩ አብራርተዋል።
በቅርቡ በመምህራን ላይ በተደረገ ግምገማ ፣ 100,000 የሚደርስ የመምህራን ዕጥረት መኖሩ መታወቁን የተናገሩት ብርሃኑ (ፕሮፌሰር)፣ አሰራሩ በከፍተኛ ደረጃ ያለውን የመምህራን ዕጥረት እንዲቀንስ የበኩልን እንደሚወጣ አስረድተዋል።
ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ሰዎችን ክፍተት ለማስተካከል ከተያዙ ዘርፈ ብዙ የማትጊያ ሥርዓቶች አንዱ፣ መምህራን በአገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ የራሳቸው ድርሻ እንዲኖራቸውና የኑሮ ውድነቱን እንዲቋቋሙ ለማድረግ፣ " የመምህራን ባንክ " ማቋቋም አንዱ እቅድ መሆኑን አንስተዋል።
ባንኩ " በአንድ ዓመት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባዋል ብለን እንጠብቃለን " ያሉት ሚኒስትሩ፣ በ2019 ዓ.ም ደግም በእርግጠኝነት ወደ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ አሰራር እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።
https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts
4232
19:14
02.04.2025
close
Reviews channel
keyboard_arrow_down
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
5.0
1 reviews over 6 months
Excellent (100%) In the last 6 months
c
**ffeenold@******.io
On the service since June 2022
25.03.202512:26
5
Everything is fine. Thank you!
Show more
New items
Channel statistics
Rating
17.7
Rating reviews
5.0
Сhannel Rating
75
Subscribers:
41.1K
APV
lock_outline
ER
1.7%
Posts per day:
0.0
CPM
lock_outlineSelected
0
channels for:$0.00
Subscribers:
0
Views:
lock_outline
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий